ቅርብ ቤተሰብ ነው cover art

ቅርብ ቤተሰብ ነው

Zelalem Gatachew Zelalem Gatachew

Created Feb 11, 2026

Lyrics

ውሻ ደግ እንሳስ ሲበዛ ታማኝ ነው
ለሰው ልጆች ወዳጅ ለጌታው ቅርብ ነው
ሲታዘዝ አይሰስት ሲጠብቅ አይሳሳ
ጌታውም ቢያባረው ከበሩ አይነሳ
ደጅ ይጸናል እንጂ ልቡን አይቀይርም
ውሻኮ ሩህሩህ ነው በመርዝ አይገደልም ።

ስንት ክፉ እያለ ለሰው የማይራራ
ወገኑን የሚገድል አረመኔ ፋራ
ለሰው ልጆች ታማኝ ሚናው ማይረሳ
እንዴት ይገደላል ውሻን የመሰለ ምርጥዬ እንስሳ ?

መጽሐፉም ይላል ጻድቅ ልብ ያለው ሰው
ለእንስሳ ይራራል
በውሻ የሚጨክን ከክፉዎች ነው
ልቦናው ደንድኗል ።

የሰው ልጆች ታሪክ በሰፊው ቢዳሰስ
የውሻ ቁርኝት ታሪኩ ቢከለስ
ውሻና የሰው ልጅ ባንድ የሚጋሩት
ስንክሳር አላቸው መቼም የማይረሱት

እናማ ጀለሴ በውሻ አትጨክን
አትምታ አትግደለው
ለሰው ልጆች ወዳጅ
ቅርብ ቤተሰብ ነው ።